ጥረትዎን ስኬታማ ለማድረግ የሚያግዙ 5 ምክሮች
ጥረትዎን ስኬታማ ለማድረግ የሚያግዙ 5 ምክሮች
1. ራስን በአንድ ነገር ሳይገድቡ ሌሎች አማራጮችን መፈለግአንድ የሙዚቃ ሙያ፣ ትወና፣ ድርሰት፣ አነቃቂ ንግግሮች እና የህክምና ሙያ ባለቤት የሆነ ሰው፤ የተለያዩ የሙያ ስብጥሮች ባለቤት መሆኑ ጥረቱ ፍሬ ማፍራቱን እንዳመላከተውና በዚያው እንዲቀጥል እንዳገዘው ተናግሯል።የባለ ብዙ ሙያ ባለቤት መሆኔ በተለይም በህይወቴ ውስጥ የተለያዩ ነገሮችን እንዳውቅ እና ስኬታማ እንድሆን አድርጎኛል ነው ያለው።በመሆኑም ሰዎች ልባቸው የሚጠቁማቸውን ፍላጎት ለማሳካት እና ጥረታቸውን ከዳር ለማድረስ በአንድ ነገር ብቻ መወሰን እንደሌለባቸው መክሯል።ኀ2. ስራዎችን መልካም ሁኔታ ላይ በምንሆንበት ጊዜ መጀመርሰዎች ጥረታቸው ስኬታማ እንዲሆን የሚሰሩትን ስራ መጥፎ ሁኔታ ባጋጠማቸው ጊዜ መጀመር እንደሌለባቸው ይመከራል።በዚህም ሰዎች በመልካም ስሜት ነገሮችን ማከናዎን ከቻሉ ጥረታቸው ፍሬ ያፈራል ነው የተባለው።ከዚህም በተጨማሪ ሰዎች ስኬት ማስመዘገብ ሲጀምሩ በውጤታማነታቸው ረክተው ጥረታቸውን ማቋረጥ አይገባቸውም፤ የመጀመሪያው ስኬት ኀለሌላ ድል መሰረት ነውና።
3. ልጅ በነበሩበት ጊዜ ምን መሆን ነበር የሚፈልጉት? አሁንስ ምን የተለወጠ ነገር አለ? የሚለውን ጥያቄ ከግምት ማስገባትብዙ ጊዜ ሰዎች በህፃንነት ዘመናቸው መሆን የሚፈልጉት የራሳቸው ምኞት ይኖራቸዋል።ሃኪም፣ መምህር፣ ጋዜጠኛ፣ የስነ ልቦና ባለሙያ፣ ደራሲ አልያም የሌሎች ሙያዎች ባለቤት የመሆን ፍላጎት በሁሉም ዘንድ ይታያል።በዚህም በልጅነታቸው የተመኙትን ሙያ አግኝተው በዘርፉ ስኬታማ ለመሆን ጥረት አድርገው የተሳካላቸው ብዙ ሰዎች ይኖራሉ። አንዳንዶቹም ስኬት ሊርቃቸው ይችላል።በህፃንነታቸው የፈለጉትን ሙያ ትተው በሌላ ሙያ የተ
ሰማሩ ሰዎች በጊዜ ሂደት በተሰማሩበት ሙያ ፍላጎት ሊያጡ ይችላሉ።ይህ ፍላጎት ማጣትም በውጤታማነታቸው ላይ ተፅዕኖ የማሳደር አቅሙ ከፍተኛ በመሆኑ፤ በተሰማሩበት መያ ስኬታማ የሆኑ ሰዎችን አርዓያ ማድረግ ተገቢ ነው።
4. ለጥረታችን የአስተውሎት ካርታ ማዘጋጀትሰዎች ይህን ማድረጋቸው ሊሰሩት ስላቀዱት ነገር ምቹ ሁኔታ በመፍጠር እርግጠኛ ያልሆኑባቸውን ነገሮች ግልፅ ለማድረግ ያስችላቸዋል።ጥረታችንን ከመጀመራችን በፊት ስራየን የምሰራው ለራሴ ነው ወይስ ለሌሎች? የሚለውን ጥያቄ ግልፅ ማድረግ ግድ ይላል።በዚህም ስኬት ላይ የሚያደርሰንን ጥረት ለመጀመር፥ ሙሉ እቅዳችን እና ፍላጎታችንን በቅደም ተከተል ማስፈር ተገቢ ይሆናል።ይህን የእቅድ ካርታ መሰረት ያደረገ ስራችንን በመጀመርም ስኬቱን በየመካከሉ እየገመገሙ መቀጠል ወሳኝ መሆኑ ተጠቁሟል።
5. የገንዘብ ችግር ከሌለ ባለን ጊዜ ምን መስራት እንወዳለን የሚለው ላይ ማተኮርሰዎች በቂ ገንዘብ እና ጊዜ ኖሯቸው ደስተኛ ወይም ስኬታማ ለመሆን ለህይወታቸው ጠቃሚ የሆነውንና በጊዜያቸው መስራት የሚፈልጉትን ስራ መምረጥ ይገባቸዋል።አንዳንዶቹ በገንዘባቸው ያላቸውን ጊዜ ተጠቅመው የበጎ አድራጎት ስራ ሊሰሩበት ይችላሉ፤ አንዳንዶቹ ደግሞ ቤተሰባቸውን ሊያዝናኑበት ይፈልጋሉ፤ ሌሎች ደግሞ የጀመሩትን ስራ ከዳር ለማድረስ አስፍላጊ ነገሮችን ሊያሟልበት ይችላሉ።በመሆኑም ሰዎች በቂ ገንዘብ ካላቸው እና ጥረታቸው ፍሬ እንዲያፈራ ካቀዱ ገንዘቡን ፈሰስ የሚያደርጉበትን ፍላጎታቸውን ማወቅ ይኖርባቸዋል ነው የተባለው።