ግሽበት (Inflation)ምን ማለት ነው ?

Published by Abreham D. on

ኢንፍሌሽን ማለት በሸቀጥና በአገልግሎት ዋጋ ላይ እድገት ወይም ጭማሪ የሚታይበት የመጠን መግለጫ ነው።

በዚህም የተነሳ አሁን ላይ ያለው ገንዘብ ወደፊት በዋጋው ግሽበት (Inflation) መጠን ልክ የመግዛት አቅሙ ዝቅ ይላል። ኢንፍሌሽን ሲጨምር ገንዘብ የመግዛት አቅሙ ይቀንሳል፣ ኢንፍሌሽን ሲቀንስ ገንዘብ የመግዛት አቅሙ ይጨምራል ወይም ባለትበት ይቆማል።

የዋጋ ግሽበትና የገንዘብ የመግዛት አቅም በተቃራኒ አቅጣጫ የሚጓዙ(Inversely Related) ናቸው አንዱ ሲጨምር ሌላኛው ይቀንሳል።

የዋጋ ግሽበት(Inflation) የሚፈጠረው ብዛት ያለው ብር ወደ ገበያው ውስጥ ሲገባና የሸቀጥ ወይም የአገልግሎት መጠን ደግሞ ሲቀንስ ወይም ባለበት ሲቆም ነው! ይህም ማለት ተጠቃሚው አንድን እቃ ለመግዛት እጁ ላይ ከዚህ ቀደም ከነበረው የበለጠ ገንዘብ ሲኖረው የእቃው አቅርቦት ግን ባለበት ከሆነ ወይም ከቀነሰ እጥረት(Scarcity) ስለሚፈጠር ተጠቃሚው ተጨማሪ ብር አውጥቶ እቃውን ይገዛል ማለት ነው። የተጠቃሚው የመግዛት ፍላጎት(Demand) ሲጨምር የገበያው የአቅርቦት መጠን ሲቀንስ የእቃ ዋጋ ይጨምራል በዚህም የተነሳ የዋጋ ግሽበት ይፈጠራል።

ሌላው ምክንያት ፋብሪካዎች የምርት ወጪያቸው ሲጨምር ባመረቱት እቃ ላይ ዋጋ ይጨምራሉ በዚህ ሰአትም የዋጋ ግሽበት ሊከሰት ይችላል።

በአንድ አመት ውስጥ የዋጋ ግሽበት መጠን 5% ከነበረ 100 ብር የመግዛት አቅሙ ወደ 95% ዝቅ ይላል ማለትም ከግሽበት በፊት የነበረ 100 ብር= ከግሽበት በኋላ ካለው 95 ብር ጋር እኩል ይሆናል ወይም 5 ብር ከጥቅም ውጭ ሆኗል ዋጋ አጥቷል ማለት ነው

source :I’m Abenezer.

ጤና ይስጥልኝ
አዳዲስ የቢዝነስ መረጃዎችና ዶክመንቶች ሲመጡ እንዲደርስዎ ይመዝገቡ
ጤና ይስጥልኝ
አዳዲስ የቢዝነስ መረጃዎችና ዶክመንቶች ሲመጡ እንዲደርስዎ ይመዝገቡ
select another Language »