አትፍራ !!

Published by Abreham D. on

ፍርሃት እጅግ ከባድ ነው። በሕይወትህ ምንም ነገር እንዳትሰራ አስሮ ያስቀምጠኃል ።ፍርሃት ልናሳካ የምናስበውን ሳይሆን ችግሮቹን አግዝፎ በማሳየት ከአላማችን እንዲሁም አዲስ ነገር ከመሞከር ያቆመናል።እጅግ የተሳካለት የቢዝነስ ሰው ወይም ታዋቂ ዘፍኝ ቢሆን እንኳን ፍርሐትን ሳያልፍ አሁን ያለበት ቦታ አልደረስም። ፍርሃት ተፈጥሯዊ ነው። የአእምሯችን ስራ ችግር እንዳይደርስብን መከላከል ነው። ሰለዚህ ችግሩ ከመድረሱ በፊት መከላከል ይፈልጋል። ስለዚህም ብዙውን ነገሮች በጣም አክብዶ ነው የሚያየው በደንብ ካላጣራን ብዙ ነገሮች ላይ ሊሸውደን ይችላል።

ለምሳሌ አዲስ ቢዝነስ ልንጀምር ስናስብ ..ትከስራለህ ብሎ ይሞግተናል። ዘፋኝ ለመሆን ስናስብ ሰው ቢስቅብህስ ፣ልምድ የለህም ይለናል። ይህንንና የመሳሰሉትን ሃሳቦችን በማንሳት አድአዲስ ነገር ከመሞከር ሊያስቆመን ይሞክራል።
ማንም ሰው በየእለቱ ፍርሃት ከእርሱ ጋር አለ። ዋናው ጥያቄ ፍርሃትን እንዴት ለጥሩ መጠቀም ይቻላል ነው። ፍርሃትን በማስወገድ አላማህን የምታሳካበት ዘዴ ለማሳየት እንሞክራለን ።

1.ሁሉ ነገር የሚጀምረው ከአንተ ነው

ከሁሉ በላይ ትልቅ ቦታ ያለው ነገር አንተ ስለራስህ ያለህ አመለካከት ነው።ስለዚህ ምን በህይወትህ ትልቅ ስፍራ አለው ? ለአለም ምን ማበርከት ትፈልጋለህ? በዙሪያህ ያሉ ሰዎችን ሕይወት ለመቀየር ምን መስራት ትፈልጋለህ?
በሕይወትህ ግልጽ የሆነ አላማ ካለህ በግልጽ ለምን እንዴት መኖር እንዳለብህ ካወቅክ የህይወት ጉዞ በስኬት የተሞላ ይሆናል ።

2. ክብርህን የምትለካበት ስርዓት ይኑርህ

በህይወት ዋጋ የምትሰጣቸውና ክብርህን የምትለካበት ስርአት ይኑርህ ።በሒወትህ ትልቅ ቦታ የምትሰጠው ነገር ምንድን ነው? ይህንን ነገር ካወክ የህይወት ጉዞህ እሱን በማስብ ላይ ይሆናል። ወደ ግብህ የምትድርስበት ዘዴ ቀይስ።  ክብርህን የማይመጥን ነገር መራቅ ወሳኝ ነው።

3.ደፋር ሁን

ከፍርሐት ውጣ ደስ የማይልህም ቢሆን ጠቃሚ ነገር ከሆነ ለማድረግ ወደኃላ አትበል። ደፋር ሁን እስከመጨረሻው ጥግ ድረስ ሞክር ። ይህ በጣም ጠንካራ ሰው እንድትሆንና በራስህ እንድትተመን ይረዳሃል። በህይወትህ ላይ የሚያመጣውን ለውጥ በመገመት የተለያዪ እድሎችን ሞክር እና ውጤት ላይ አድርሳቸው።”ደፍር እና ጭስ መውጫ አያጣም “እንደሚባለው


4.እርምጃ ውሰድ

ብዙውን ግዜ የምንፈራው በመጭው ግዜ ሊያጋጥመን የሚችለውን ነገር ነው። ነገር ግን ዋናው ማድረግ ያለብን ትኩረታችንን ማሳካት የምንችለው ነገር ላይ ነው።
ከዛም እርምጃዎችን መውስድ ነው።እርምጃ መውሰድ ፍርሃትን ለማስወገድ ይረዳናል። ምንም ፍርሀትና ጥርጣሬ ቢኖረንም በማድረግና በመሞከር  ፍርሃታችንን ለማሸነፍ ለመቆጣጠር ይረዳናል።

5. ወሳኝ ሁን

አንድ ነገር ለመወሰን ፍርሃት ወይንም አልችለውም ይሆናል የሚል ጥርጣሬ ከያዘንና ከተውነው ሌላ ፍርሃት ሰለሚያመጣብን በሒወታችን የማንለወጥ በህይወታችንን መምራት የማንችል እንሆናለን። ትልቁ ደፍርነት መገለጫ ፍርሃትን መጋፈጥ ነው። መሳሳት ምንም ማለት እንዳልሆነ በማወቅ ውሳኔ መስጠት ነው።

6. ፍርሃትን መመርመርና ራስህን ማውራት 

ፍርሃት ችግር እንዳያጋጥመን አእምሮችን የሚከላከልበት ዘዴ ነው። የምንሞክረው ነገር ለኛ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል ነገር ግን አእምሯችን ግን አዲስ በመሆኑ ስላልተረዳው ብቻ እንዳንሰራው ይከለክለናል። በዚህን ግዜ ነገሩን መመርመርና ጠቃሚ ከሆነ ከራሳችን ጋር በማውራት ይህንን ነገር መሞከርና ራሳችንን መቆጣጠር ።

በሕይወታቸው ትልቅ ስኬት ላይ የደረሱ ሰዎች ፍርሃታቸውን በማሸነፍ እስከ ጥግ ድረስ የሄዱ ናቸው። የተለየህ ሁን ውስጥህን በማየት ስጦታህን አውጣው። በውስጥህ ያለውን ሐይልና እውቀት ፍርሃትን በማሸነፍ አከባቢህ ይሉትን ሰዎች እርዳና ቀይር! የምታደንቃቸው ሰዎች ትልቅ ስም ያገኙት ፍርሃታቸውን በማሸነፍ አላማቸውን ያሳኩ ናቸው ። ስለዚህ በመሞከርህ ምን ታጣለህ ? ሞክር 

select another Language »