የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ አወጣጥ

የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ አወጣጥ

1.የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማውጣት ስለሚገባቸው

የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የመውሰድ ወይም የማውጣት ግዴታ ያለባቸው፡-
1) ግለሰብ ነጋዴ፣
2) ተቀጣሪ ሠራተኛ፣
3) ግብር የሚከፈልበት ገቢ የሚያስገኝ የሙያ ሥራ የሚሠራ ሰው፣
4) መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣
5) በንግድ ሥራ የተሰማሩ የሃይማኖት ድርጅቶች፣
6) ኩባንያዎች፣ Aክሲዮን ማኀበራት፣ የሽርክና ማኀበራት፣ የEሽሙር ማኀበራት /joint venture/ Eንዲሁም በንግድ ሥራ የተሠማሩ ማናቸውም ማኀበራት ናቸው፡፡
7) የፌዴራል መንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የወጪ መጋራት ተጠቃሚዎች/ተማሪዎች

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ለማግኘት መቅረብ ያለባቸው ማስረጃዎች

1) በግለሰብ ለሚካሄድ የንግድ ሥራ፣ በተቀጣሪና የሙያ ሥራ በሚሠራ ሰው፣
ሀ/ የግብር ከፋዩ የከተማ ቀበሌ ወይም የቀበሌ ገበሬ ማኀበር መታወቂያ፣
ለ/ የAመልካቹ /የግብር ከፋዩ/ ከስድስት ወር ወዲህ የተነሣው ፎቶግራፍ፣ E:/Manuals u0026amp; directives/TIN 2
ሐ/ Aመልካቹ የቤተሰቡን ንግድ የወረሰ Aካለ መጠን ያልደረሰ ልጅ ሞግዚት ከሆነ ይህንኑ የሚያረጋጋጥ ከፍ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ
ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
2) ኩባንያዎች፣ Aክሲዮን ማኀበራት፣ የሽርክና ማኀበራት፣ የEሽሙር ማኀበራት /joint venture/ Eንዲሁም በንግድ ሥራ የተሠማሩ ማናቸውም ማኀበራት፣
ሀ/ የማኀበር መመስረቻ ጽሑፍና መተዳደሪያ ደንብ፣
ለ/ የድርጅቱ ዋና ሥራ Aስኪያጅ ከስድስት ወር ወዲህ የተነሣው ፎቶግራፍና በግሉ ያወጣውን የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣
ሐ/ Aመልካቹ ወኪል ከሆነ ስለውክልናው የተሰጠውን ሕጋዊ ማስረጃ፣
መ/ ከማኀበርተኞቹ መካከል የውጭ Aገር ዜጋ ካለ ማንነቱን የሚገልጽ ፓስፖርት Oሪጅናልና ፎቶኮፒ Eንዲሁም ከIንቨስትመንት ጽ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ፣
ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
3) የመንግስት የልማት ድርጅቶች፡-
ሀ/ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣
ለ/ ድርጅቱ የተቋቋመበትን ደንብ፣
ሐ/ የድርጅቱ ሥራ Aስኪያጅ ምደባ ደብዳቤ፣
መ/ የሥራ Aስኪያጁ የቀበሌ መታወቂያና ከስድስት ወር ወዲህ የተነሣው ፎቶግራፍና በግሉ ያወጣውን የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣
ሠ/ የንግድ ፈቃድ ፎቶኮፒ፣
ረ/ Aመልካቹ ወኪል ከሆነ ስለውክልናው የተሰጠውን ሕጋዊ ማስረጃ፣ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
4) የመንግስት ባለበጀት መስሪያ ቤቶች
ሀ/ የማቋቋሚያ Aዋጅ ወይም ደንብ፣
ለ/ መስሪያ ቤቱ የሚወክለው ሰው የውክልና ደብዳቤና የግለሰቡ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣
5) መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች
ሀ/ የፍትሕ ሚኒስቴር የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣
ለ/ የሥራ Aስኪያጅ ምደባ ደብዳቤና የግሉን የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ E:/Manuals u0026amp; directives/TIN 3

3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ለማግኘት መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎችና ግዴታዎች

ማንኛውም ሰው፡-
1) የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ለማግኘት በባለሥልጣኑ የተዘጋጀውን ቅጽ ሞልቶ ማቅረብና የጣት Aሻራ የመስጠት፣
2) የንግድ ሥራ ፈቃድ ለማውጣት የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት ከባለሥልጣኑ በቅድሚያ የማግኘት፣
3) ግለሰቡ የተለያየ የንግድ ዘርፍ ወይም ቅርንጫፎች በተለያዩ ቦታዎች ቢኖሩትም Aንድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ብቻ የማውጣት፣
ግዴታ Aለበት፡፡

4. የጣት Aሻራ መስጠት የማይጠበቅባቸው ድርጅቶች

በዚህ መመሪያ Aንቀጽ 5(1) የተደነገገው ቢኖርም የሚከተሉት በተቋም ደረጃ ብቻ የጣት Aሻራ መስጠት Aይጠበቅባቸውም፡፡
1) የመንግስት ባለበጀት መስሪያ ቤቶች፣
2) የመንግስት የልማት ድርጅቶች፣
3) የንግድ ማኀበራት /የAክሲዮን ማኀበራት፣ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኀበር፣ የEሽሙር ማኀበር፣ የሽርክና ማኀበራት…../
4) መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች
5) የማንኛውም ሰው ወይም ድርጅት ወኪል ስለወከለው ሰው ወይም ድርጅት በመወከል፣ ራሱን ችሎ የንግድ ወኪል በመሆን ፈቃድ Aውጥቶ የሚሠራ ካልሆነ በስተቀር፡፡

5. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ስላልወሰዱ ግብር ከፋዮች

1) የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸውና በማንኛውም የንግድ ሥራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ሆኖም በተለያዩ ምክንያቶች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያልወሰዱ E:/Manuals u0026amp; directives/TIN 4
ግብር ከፋዮች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት ለማግኘት የምዝገባ ቅጽ ሞልተው በAንቀጽ 5 የተመለከቱትን ማስረጃዎች ማቅረብ Aለባቸው፡፡
2) በAንቀጽ 7 ከተመለከቱት በስተቀር በዚህ Aንቀጽ ንUስ Aንቀጽ (1) የተጠቀሱት ግብር ከፋዮች የጣት Aሻራ በመስጠት የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት ማግኘት ይኖርባቸዋል፡፡

6. የምዝገባ ቦታዎች

1) የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) የሚሰጠው Eንደ Aግባብነቱ በፌዴራል ወይም በክልል ወይም በከተማ Aስተዳደር ገቢ ሰብሳቢ መስሪያ ቤት ይሆናል፣
2) ማንኛውም ሰው በሚኖርበት ወይም የንግድ ሥራው በሚገኝበት Aካባቢ ባለው የገቢ ሰብሳቢ መስሪያ ቤት በመቅረብ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር Eንዲሰጠው መጠየቅ ይችላል፣
3) ማንኛውም ሰው የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ለማግኘት መመዝገብ ያለበት ዋና መስሪያ ቤቱ በሚገኝበት Aካባቢ ባለው የገቢ ሰብሳቢ መስሪያ ቤት ይሆናል፣
4) ግብር ከፋዩ በAንድ ወይም በተለያዩ የንግድ ዘርፎች ላይ የተሰማራ፣ በተለያዩ ዞኖች ወይም ክልሎች ወይም የከተማ Aስተዳድሮች ውስጥ የንግድ ሥራ የሚያካሂድ ከሆነ የሁሉንም Aድራሻ ማስመዝገብ ይኖርበታል፣
5) በAንድ ቦታ የተሰጠ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ምስክር ወረቀት ለፌዴራል Eንዲሁም ለሁሉም ክልልና ከተማ Aስተዳደር የሚያገለግል ይሆናል፡

ጤና ይስጥልኝ
አዳዲስ የቢዝነስ መረጃዎችና ዶክመንቶች ሲመጡ እንዲደርስዎ ይመዝገቡ
ጤና ይስጥልኝ
አዳዲስ የቢዝነስ መረጃዎችና ዶክመንቶች ሲመጡ እንዲደርስዎ ይመዝገቡ
select another Language »