የንግድ ወጭ ስሌት

የንግድ ወጭ ስሌት

 

ያለአግባብ ወጭና ብክነት የሀብት እጥረት እንደሚያስከትሉ በርካታ ሰዎች በቂ ግንዛቤ የላቸውም፡፡ አምራቹ/አገልግሎት ሰጭው ለወጭ ግምት እንዲኖራቸውና ስለእነሱም በስልታዊ ዘዴ እንዲያስቡበት፣ ቀለል ያለ የወጭ ስሌት እንዲጠቀሙ ማድረግ ጥሩ አማራጭ ነው፡፡

የወጭ ስሌት ጠቅላላ የምርቱን/አገልግሎቱን ማምረቻና ለመሸጫ የሚወጣውን ወጭ ማስላት ያጠቃልላል፡፡

ይህ የወጭ ስሌት የንግድ ሠራን ለማሻሻል በሚከተሉት መንገዶች ይረዳል፡፡

 • ዋጋን ለመተመን ይረዳል፣
 • ወጭን ለመቆጣጠርና ለመቀነስ ይረዳል፣
 • የወጭ ስሌት የወደፊት እቅድ ለማቀድ ይረዳል፣
 • የወጭ ስሌት የተሻለ ውሳኔ ለመስጠት ይረዳል፣
 • የወጭ ስሌት ብድር ለማግኘት የንግድ እቅድ ለማዘጋጀት ይረዳል፡፡

 

ደረጃዎች

 1. የወጭን ክፍሎች መለየት፣
 2. ወጭዎችን መዘየድ፣
 3. ተለዋዋጭ ወጭዎችን ማስላት፣
 4. ቋሚ ወጭዎችን ማስላት፣
 5. የአንድ ምርት /አገልግሎት/ ጠቅላላ ወጭዎችን ማስላት፣
 6. ዋጋዎችን መተመን፣ የማጣሪያ ዋጋን ማስላት፣

 

 

 

 

 

 

 1. የውጭ ክፍሎችን መለየት
 • በዚህ ድርጅት ውሰጥ ምን ምን ዓይነት የወጭ ክፍሎች ሥራ ላይ ይውላሉ?
 • ምርት

የሰው ኃይል

ጥሩ እቃዎች

የኤሌክትሪክ፣ ትራንስፖርት፣ ኪራይ፣ ውሃ፣ ወዘተ…

ሌሎች …. ወዘተ

 

 

 • ሥራ አመራር

የሰው ኃይል፣ የሥራ ፈጣሪው ደመወዝ

የጽህፈት መሣሪያ

ስልክ፣ ኪራይ፣ ኤሌክትሪክ፣ መድን፣ ወዘተ…

መሣሪያዎች

ሌሎች

 

 

 • ሽያጭ

ለህዝብ ማሳወቅ፣ ማስፋፋት፣ ኮሚሽን ወዘተ…

 

 

 

 • ገንዘብ /ፋይናንስ/

ወለድ

 

 

 • ሁሉንም ወጭዎች በቀላል ሰንጠረዥ መዘርዘር፣ ለምሳሌ ያህል እቃዎች፣ ኤሌክትሪክ ————————–
የእቃው ዓይነት ብዛት ወጭ ምርመራ
ዱቄት 10 ኪ.ግ በኪ.ግ 2 ብር /ተለዋዋጭ/
ስኳር 10 ኪ.ግ በኪ.ግ 2 ብር /ተለዋዋጭ/
    /ተ ወይም ቋ/
 • ማሽን፣ መሣሪያ፣ የእጅ መገልገያዎች
የማሽን/የመሳሪያው ዓይነት ወጭ የአገልግሎት

ዘመን

ምርመራ
….     /ተ ወይም ቋ/
የዱቄት ማዋሃጃ 6000 ብር 5 ዓመት ቋሚ
     

 

 

 

          ለእያንዳንዱ ሠራተኛ የጉልበት ወጭን በሰዓት ማስላት

ስም የስራ ድርሻ ወጭ በወር ዋጋ በሰዓት
  አስተዳደር   ቋሚ
  ምርት ክፍል   /ተ ወይም ቋ/
     

        የሰው ኃይል

ምርቱን/አገልግሎቱን ለመጨረስ የሚያስፈልገውን የሥራ ሰዓትና የሠራተኛ ቀጥታ ወጭዎችን ማስላት

ደረጃ ሰዓት የሚያከናውን ሰራተኛ ዋጋ
       
       
     
 • የምርት ሂደት

በምርት ሂደት በየደረጃው ለሠራተኛው የሚወጣው ወጭ የሚሰላው ደረጃውን በሚፈፅመው ሰራተኛ የሰው ኃይል ዋጋ በሰዓት በሚያስፈልግው ሰዓት በማባዛት ነው፡፡

 1. ወጭዎችን መዘየድ

በቋሚና ተለዋዋጭ ወጭዎች ፅንሰ ሀሳብ ላይ ውሳኔ ላይ ለመድረስ አምራቹ/አገልግሎት ሰጭው በኪራይና በዱቄት ወጭ/ምሳሌ በዳቦ ቤት/መካከል ስላለው ልዩነት አንዲያስብበት ማድረግ፣

 • ቋሚ ወጭዎች ማንኛውንም ምርት ለማምረት የሚያስፈልጉ ወጪዎች ድምር ናቸው፡፡ የምርቱ/የአገልግሎት መጠን ቢጨምር የማይለዋወጡ ናቸው፡፡ ቋሚ ወጪዎች ሁኔታዎችን ለማመቻቸት የሚወጡ ወጪዎች፣ የተወሰኑ ጠቅላላና አስተዳደራዊ ወጭዎችን፣ ወለድና የእርጅና ቅንሽ ወጭዎችን ይጨምራሉ፡፡
 • ተለዋዋጭ ወጪዎች ተጨማሪ አሀዶችን ከማምረት ጋር ያገናኛሉ፡፡ ከምርቱ/ከአገልግሎቱ መጨመር ጋር የሚለዋወጡ ናቸው፡፡ ቀጥተኛ የእቃ/ማቴሪያልና የሠራተኛ ወጭዎችን፣ የትራነሰፖርትና የሽያጭ ኮሚሽን ወጭዎችን ይጨምራሉ፡፡ ተለዋዋጭ ወጪዎች የአንዱ እቃ ወጭ፣ አንድ ተጨማሪ ነገር ለማምረት የሚወጡ ወጭዎች ናቸው፡፡
 • ጠቅላላ ወጪ የቋሚ ወጭዎችና የተለዋዋጭ ወጭዎች ድምር ነው፡፡ ይህ ፅንሰ ሃሳብ የሚያመለክተው /በውል፣ ቃል በመግባት ወዘተ../ የቋሚ ወጭዎች ሊቀነሱ የሚችሉ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ብቻ ነው፡፡ በዚህ መርህ የወጭዎች ምደባ በምርቱ ዓይነት የሚወሰን ነው፡፡ በተጨማሪም የተወሰኑ በምርት አሀድ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ተለዋዋጭ ወጭ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ኤሌክትሪክ ለቢሮ ሕንፃ ቋሚ ወጭ ነው፡፡ ነገር ግን ልብ የሚመቱ የተወሰኑ ደንቦች አሉ፡፡
 • ጥሩ እቃዎች ሁልጊዜ ለተለዋዋጭ ወጭዎች ምክንያት ናቸው
 • ምርታማ ሥራ በቀጥታ ለምርቱ/ለአገልግሎቱ የሚወጡ
 • ቀጥተኛ የሠራተኛ ወጭዎች ተለዋዋጭ ወጭዎች ናቸው
 • አስተዳደራዊ ወጭዎች በአብዛኛው ቋሚ ወጭዎች ናቸው
 • የቋሚና ተለዋዋጭ ወጭዎች ምሳሌ
   

ቋሚ ወጭዎች

ተለዋዋጭ ወጭዎች
ዳቦ ቤት አናፂ ቸርቻሪ አገልግሎት
አርዕስት አስተዳደራዊ ወጭዎች/

/ስልክ፣ ፋክስ/

የጽህፈት መሣሪያዎች

ኪራይ፣ መብራት፣ ውሃ

ትራንስፖርት፣

 

የሕዝብ አገልግሎት

እድሳት

የማስታወቂያ ስራ

የእርጅና ቅናሽ

ሌሎች 

ድቄት

ስኳር

እንቁላል

ጨው

 

 

ወተት

መብራት

ውሃ

እንጨት

ማጠፊያ

ቅብ

መፈቻ

የቅርንፉድ

ሚስማር

የሚያያዝ

ሙጫ

 

…..

መብራት

ውሃ

የሸቀጦች

ወጭ

በአገልግሎት

ጥቅም

የሚውሉ

እቃዎችና

መለዋወጫዎች

 

መብራት 

የሰው ኃይል የስራ ፈጣሪው ደመወዝ ምንዳ ደመወዞች /የአንዱ ነጠላ ምንዳ ዋጋ አይደለም/ በተመረተው ልክ ደመወዝ በተመረተው ልክ ደመወዝ የሽያጭ ኮሚሽን /ክፍያ/ የተሰጠው አገልግሎት ልክ ክፍያ

ሁሉንም ወጭዎቹን እንደተለዋዋጭ ወይም ቋሚ አንድ በአንድ እንዲመድብ አምራቹን/አገልግሎት ሰጭውን ይጠይቁ፡፡ በቋሚና በተለዋዋጭ ወጭዎች መካከል ያለውን ልዩነት መረዳቱን ያረጋግጡ፡፡ ይህ ከሆነ ብቻ ነው የእያንዳንዱን ምርት/አገልግሎት ቋሚና ተለዋዋጭ ወጭዎችን በትክክል ማስላት የሚቻለው፡፡ ይህም ዋጋ ለመተመን መሰረት ይሆናል፡፡

 1. ለእያንዳንዱ ምርት/አገልግሎት ተለዋዋጭ ወጪዎችን አስላ ተለዋዋጭ ወጭዎች
 

የእቃው ዓይነት

 

ዋጋ /የግዢ ዋጋ/

የተጠቀመበት ብዛት በምርት/ለአገልግሎት ለአንድ ምርት/አገልግሎት የወጣው ወጭ
ጥሬ እቃዎች      
ዱቄት 2 ብር በኪ.ግ 10ኪ.ግ/በ100 ኬኮች 20 ብር/100 ኬኮች
ስኳር 5 ብር በኪ.ግ 1ኪ.ግ/100 ኬኮች 5 ብር /100 ኬኮች
     
የሠራተኛ ወጭዎች      
የትራንስፖርት      
     
/1/ ተለዋዋጭ ወጭዎች በአንድ ምርት/አገልግሎት መጠን 25 ብር/100 ኬኮች

0.25 ብር /ኬክ

የተመረተው ምርት በጣም አነስተኛ ነገር ከሆነ፣ /ምሳሌ ኬክ/ እና በተወሰነ ጊዜ በሺህ የሚቆጠሩ ምርቶች ከተመረቱ፣ ለአንዱ ምርት የተጠቀሙበትን ጥሬ እቃ መጠን መጥቀስ አስፈላጊ አይሆንም፡፡ ይልቁንም በ100 ወይም በ1000 ነጠላ ምርቶች የተጠቀሙበትን መጠን ማስላት ይሻላል፡፡ ነገር ግን በመጨረሻ ተለዋዋጭ ወጭዎች በአንዱ ነጠላ ምርት መስተካከል አለባቸው /ምሳሌዎችን/ ይመልከቱ፡፡

 1. ለእያንዳንዱ ምርት/አገልግሎት ቋሚ ወጭዎችን ማስላት

ቋሚ ወጭዎች

የወጪ አርዕስት ወጭ/በወር
ኪራይ  
ደመወዞች/አስተዳደራዊ/  
የሕንፃ የእርጅና ቅናሽ፣ የማሽኖች ….  
   
/2/ ጠቅላላ ቋሚ ወጭዎች  
/3/ ወርሃዊ ምርት /በነጠላ/  
/4/ ቋሚ ወጭ በአንዱ ነጠላ ምርት/ አገልግሎት /2/3/  

 የእርጅና ቅናሽ የንብረት ጠቀሜታ/አገልግሎት ፅንሰ ሃሳባዊ /ትወራዊ/ ዋጋ ነው፡፡ ከእርጅና ቅናሽ ማስላት ልዩ ልዩ ዘዴዎች አንዱ እና ቀላል መንገድ ንብረቱ የተገ]ዛበትን ዋጋ ለአገልግሎት ዘመኑ ማካፈል ነው፡፡

ለምሳሌ አንድ ማሽን ብር 6,000 ወጭ ሆኖ፣ የተገዛ ከሆነ እና ለ5 ዓመት የሚያገለግል ከሆነ የእርጅና ቅናሽ በዓመት 6,000 ብር ሲከፈል ለ5 ዓመት ይሆናል 1,200 ብር በዓመት ማለት ነው፡፡

የእርጅና ቅናሽ በወር 1,200 ብር ሲካፈል ለ12 ወራት ይሆናል በወር 100 ብር ማለት ነው፡፡

የንግድ ስራው ከአንድ ዓይነት በላይ ምርቶችን የሚያመርት ከሆነ በተቻለ መጠን ቋሚ ወጭዎች ለየምርቶቹ ዓይነት መከፈል/መሰላት አለባቸው፡፡ ለእያንዳንዱ ነጠላ ምርት የጠቅላላ ተለዋዋጭ ወጭዎች ግንኙነት የቋሚ ወጭዎችን በየምርቱ ለማስላት/ ለመገመት መሰረት ይሆናል፡፡

 1. ጠቅላላ ወጪዎችን በአንዱ ምርት መጠን ያስሉ?
 • በአንድ ምርት ልክ ተለዋዋጭና ቋሚ ወጭዎችን ይደምሩ፣
/1/ ተለዋዋጭ ወጭ በነጠላ ምርት/አገልግሎት  
/4/ ቋሚ ወጭ በነጠላ ምርት/አገልግሎት  
/5/ ጠቅላለ ወጭ በአንዱ ምርት/አገልግሎት መጠን /1+4/  
 1. ወጭን ማስላት ንግዱን እንዴት ያሻሽላል?
  • የዋጋ ምደባ /ትመና/

አምራቹ/አገልግሎት ሰጭው ዋጋዎችን ለመተመን የሚከተሉት መረጃዎች ያስፈልጉታል፡፡

 • የእሱ ወጪዎች
 • የተወዳዳሪዎች ዋጋዎች
 • ደንበኞች ምን ያህል ለመክፈል ፈቃደኞች ናቸው፡፡

በአጠቃላይ ዋጋ መሆን ያለበት፣

 • ደንበኞች ለመግዛት እንዲችሉ በተቻለ መጠን ለመሳብ አነስተኛ መሆን አለበት
 • ለንግዱ በተቻለ መጠን ከፈተኛ ትርፍ የሚያስገኝ መሆን አለበት ትርፍ ለማግኘት፣ የመሸጫ ዋጋው ከጠቅላላው የማምረቻ ዋጋ መብለጥ አለበት፡፡ ስለዚህ ጠቅላላ የማምረቻ ዋጋን ማወቅ የመሸጫ ዋጋን ለመወሰን ይረዳል፡፡

ይህንንም ለማድረግ ሁለት መንገዶች አሉ፡፡

 • አምራቹ/አገልግሎት ሰጭው በማምረቻው ዋጋ ላይ የተወሰነ ትርፍ በመጨመር የመሸጫ ዋጋን ይተምናል፡፡
 • አምራቹ/አገልግሎት ሰጭው የእሱን ተወዳዳሪዎች ዋጋ ማየትና ከሱ ዋጋ ጋር ተወዳዳሪ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት፡፡ ነገር ግን የእሱ ዋጋ የጠቅላላ ወጭውን መሸፈን ማረጋገጥ አለበት፡፡
  • የዋጋ ቅናሽ ማድረግ

የዋጋ ቅናሽ ሲደረግ የንግድ ሥራው በትርፋማነቱ መቆየቱን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡

የዋጋ ቅናሽ የማድረግ ስሌት በሚደረግበት ጊዜ የሚከተሉት ደረጃዎች መካተት አለባቸው፡፡

 1. የንግዱን ጠቅላላ ቋሚና ተለዋዋጭ ወጭዎችን አግባብ ባለው ጊዜ ውስጥ በትክክል መለየት፣
 2. ቋሚ ወጭ ሳይቀነስ የሚገኘው ትርፍ እንደሚከተለው ይሰላል፡፡

የትርፍ መጠን በአንድ ምርት/አገልግሎት = የአንዱ የሽያጭ ዋጋ – የአንዱ ተለዋዋጭ ወጪ ይህ መጠን ቋሚ ወጭዎችን ለመተካትና እንደዚሁም ለንግዱ መንቀሳቀሻ የሚሆን ትርፍን የሚያካትት ነው፡፡

 1. የማጣሪያ የሽያጭ መጠን ለመወሰን እንደሚከተለው ይሰላል፡፡

የማጣሪያ ሽያጭ መጠን = ጠቅላላ ቋሚ ወጭዎች/ከአንድ ምርት የሚገኝ ትርፈ ቋሚ ወጭ ሳይቀነስ ያለው የሽያጭ መጠን ከማጣሪያው ሽያጭ መጠን የሚበልጥ ከሆነ ንግዱ ትርፋማ ነው ማለት ነው፡፡ ካልሆነ ግን ንግዱ ኪሳራ ላይ ነው ማለት ነው፡፡

 • እስትራቴጂዎች /ስልቶች/

በአጠቃላይ የምርቱ/የአገልግሎቱ የሽያጭ ዋጋ ያንን ምርት ለማምረት ከወጣው ተለዋዋጭ ወጭ መብለጥ አለበት፡፡ እንደዚሁም የቋሚ ወጭውን ድርሻ ለመሸፈን በቂ መሆን አለበት፡፡

የሽያጭ ዋጋ ጠቅላላ ወጭዎችን የማይሸፍን እና ተለዋዋጭ ወጭዎችን የሚሸፍን ሊሆን ይችላል፡፡ ለዚህ ተስማሚው ስልት ሽያጭን የመጨመር እርምጃዎችን ተግባራዊ ማድረግ ነው፡፡ የገበያ ድርሻው የማይጨምር ከሆነ ቋሚ ወጭዎችን መቀነስ ያስፈልጋል፡፡

ነገር ግን የአንድ ምርት/አገልግሎት የሽያጭ ከተለዋዋጭ ወጭ በታች ከሆነ ሽያጭን መጨመር ትርጉም አይሰጥም፡፡ ተጨማሪ አሀድ በመሸጥ አምራቹ/አገልግሎት ሰጭው ኪሳራውን ይጨምራል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ሽያጭን የመጨመር እርምጃ አግባብነት ያለው ስልት አይደለም፡፡ አምራቹ/አገልግሎቱን ሰጭው ተለዋዋጭ ወጭዎችን መቀነስ አለበት፡፡ ቋሚ ወጭዎችን መቀነስ ፈፅሞ አስፈላጊ ባይሆንም በቂ አይደለም፡፡

 

 

 

 • ወጪዎችን የመቀነሻ መንገዶች

በርካታ ሰዎች ስለ ወጭ በቂ ግንዛቤ ባለመኖራቸው ውስን ሃብትን ሲያባክኑ ይታያሉ፡፡ አምራቹን/አገልግሎት ሰጭውን በውጭ ላይ ትኩረት እንዲኖረው ማድረግ ሁልጊዜ ጥሩ ነጥብ ነው፡፡ በተለይም ጥራቱን ሳይቀንስ ወጭን ለመቀነስ አቅሙ ካለው /ተለዋዋጭና ቋሚ ወጭዎችን/ በማንኛውም ሰው በቀላሉ ሊከናወኑ የሚችሉ በጣም ቀላልና የተለመዱ መንገዶች የሚከተሉት ናቸው፡፡

 • አለአግባብ የሚወጣውን ወጭ ማቆም መቆጣጠር
 • የእጅ መገልገያ መሣሪያዎችና እቃዎችን በጥንቃቄ መያዝ፣ መገልገያዎችን ማፅዳት፣
 • አላስፈላጊ የሆኑ መብራቶችን ማጥፋት፣
 • በወቅቱ የማትጠቀምበት ማሽንን ማቆም፣
 • ፈጥነህ ስራ፣ ነገር ግን ጥራቱን ጠብቅ፣
 • ….

እንደሁኔታው አመቺ የሆኑና የተሻሉ መፈትሔዎች መፈለግ አለባቸው፡፡

ተለዋዋጭ ወጭዎችን ለመቀነስ፣

 • በርካሽ የሚያቀርቡ አቅራቢዎችን ፈልግ ነገር ግን በተመሳሳይ ወይም በላቀ ጥራት፣
 • ለብዙ ትዕዛዝ ሌሎችና ተባባሪዎችን ፈልግ፣
 • ወጭዎችን ከሌሎች ጋር ተካፈል፣
 • የእስቶክ /የክምችት/ ደረጃውን መጠነኛ አድርግ የክምችት ከፍተኛ መሆን የወለዱ ወጭ ከፍተኛ መሆንን ያስከትላል፡፡ ነገር ግን የክምችት አነስተኛ መሆን ከክምችት ባዶ የመሆን እድሉ ከፍተኛ ይሆናል፡፡
 • የሥራ ቦታ ሊይአውት አሻሽል፣ ጥሩ የወርክሾፕ ሌይአውት ማለት የምርቱ ሂደት እንቅስቃሴ በትክክል እንዲከናወን ይረዳል ያፋጥናል፡፡

ቋሚ ወጭዎችን ተለዋዋጭ ማድረግ

 • የመሣሪያ ወይም የሰው ሀይል ሀብት አጠቃቀም አነስተኛ ከሆነ እነዚህን አገልግሎቶች /በመከራየት መጠቀም ስሜት የሚሰጥ ነው፡፡ ስለዚህ አምራቹ/አገልግሎት ሰጭው እነዚህን መሣሪያዎች ወይም የሰው ኃይል የሚፈለገው ጊዜ መከራየት/መቅጠር ወይም መግዛት ይኖርበታል፡፡

 

ጤና ይስጥልኝ
አዳዲስ የቢዝነስ መረጃዎችና ዶክመንቶች ሲመጡ እንዲደርስዎ ይመዝገቡ
ጤና ይስጥልኝ
አዳዲስ የቢዝነስ መረጃዎችና ዶክመንቶች ሲመጡ እንዲደርስዎ ይመዝገቡ
select another Language »