የራስዎን ሥራ ያስተዳድሩ
የራስዎን ሥራ ያስተዳድሩ
በተደረገው ጥናት መሰረት በኢትዮጵያ የንግድ ድርጅቶች በጣም ተስማሚና አስተማማኝ የገበያ ስትራቴጂዎች ከዚህ በታች ይገለፃሉ፣ አስተያየትም ይሰጥባቸዋል፡፡
ሀ/ የምርት ስትራቴጂዎች
አንዳንድ የንግድ ድርጅቶች በስፋት የማምረትና ስትራቴጂ ማጎልበት ይችላሉ፡፡
ለ/ የዋጋ ትመና ስትራቴደዎች
በአንድ አዲስ ምርት ላይ የዋጋ ቅናሽ ማድረግ ምርቱን ለማስተዋወቅና ሸማቾችን ለመሳብ ሁነኛ መሳሪያ ነው፡፡ ይህ ግን ለተወሰነ አጭር ጊዜ ብቻ መሆን አለበት፡፡
ሐ/ የማስተዋወቅ ስትራቴጂዎች
በኢትዮጵያ ውስጥ የምርት ማስታወቂያ ማሰራት በጣም ውድ ነው፡፡ ስለዚህ የንግድ ድርጅቶች የበለጠ ውጤታማና ሊሰራላቸው የሚችል የማስተዋወቅ ዘዴ መፈለግ አለባቸው፡፡
መ/ የአስተሻሸግ ስትራቴጂዎች
አስተሻሸግ በረጅም ጊዜ ግብይት ውስጥ የመወዳደሪያና አስፈላጊ ጉዳይ ነው፡፡ ስትራቴካዊ አስተሻሸግ ጥራትን፣ አመቺነትንና አስተማማኝነትን ሊገልፅ ይችላል፡፡
ሠ/ የሽያጭ ስትራቴጂዎች
ደንበኛን ለመለየትና እንዴት ማርካት በበለጠ መንገድ መያዝ እንደሚቻል ለማወቅ ገበያውን በየክፍሉ ማጥናት ይቻላል፡፡
ሠ/ የውድድር ስትራቴጂዎች
የንግድ ምክር ቤቶችን እና የንግድ ማህበራት አባል መሆን ከተወዳዳሪዎች ጋር መቀላቀያና ስኬታማ የሆኑ ድርጅቶች የንግድ ሥራቸውን እንዴት እንደሚያካሂዱ ለመማር አንዱ መንገድ ነው፡፡
ረ/ የጥራት ጋር የተያያዙ ስትራቴጂዎች
ጥራትን በተመለከተ የንግድ ድርጅቶች በትንሹ ማድረግ የሚገባቸው አሁን ያለውን ጥራት እንደተጠበቀ እንዲቆይ የሚያስችል ፖሊሲ ማውጣትን እንደ አጠቃላይ ስትራቴጂ መከተል አለባቸው፡፡
ድርጅት ማስተዋወቅ
ማስተዋወቅ የግብይት አንዱ ዓላማ ሲሆን ምርትዎን ለገበያው ለማሳወቅ፣ ለማሳመንና ለማስገንዘብ የሚጠቀሙበት ነው፡፡ ማስተዋወቅን በሚገባ ማቀድ ለንግድዎ ስኬታማነት ወሳኝ ነው፡፡
የንግድ ወጭ ስሌት
ያለአግባብ ወጭና ብክነት የሀብት እጥረት እንደሚያስከትሉ በርካታ ሰዎች በቂ ግንዛቤ የላቸውም፡፡ አምራቹ/አገልግሎት ሰጭው ለወጭ ግምት እንዲኖራቸውና ስለእነሱም በስልታዊ ዘዴ እንዲያስቡበት፣ ቀለል ያለ የወጭ ስሌት እንዲጠቀሙ ማድረግ ጥሩ አማራጭ ነው፡፡
ገንዘብ መቆጠብ
ቁጠባ ዛሬ ላይ ሆነን ነገን በማሰብ ከምናገኘው ገቢ በተወሰነ መጠን ወይም መቶኛ ቀንሰን የምናስቀምጠውና ለፍጆታ የማናውለው ገንዘብ ነው፡፡ ቁጠባ ለነገ የተሻለ ህይወት፣ ለእርጅና ዘመን፣ ወደፊት ለሚያጋጥመን የገንዘብ እጥረት፣ ለልጆቻችን የወደፊት የከፍተኛ ትምህርት ፍላጎት፣ ሊያጋጥሙን ለሚችሉ አደጋዎች መቋቋሚያ ወዘተ. ፍላጎቶቻችን ሁሉ ለመጠቀም እንድንችል ዛሬ የምናስቀምጠው ገንዘብ ነው፡፡