የሥራ እቅድ ያዘጋጁ
የንግድ ሥራ አቅድ
የንግድ ሥራ ዕቅድ፣ ስኬታማ ንግድ ለመጀመር፣ ለመገንባትና ለመምራት በጣም አስፈላጊ ሰነድ ነው፡፡ እንዲሁም አስፈላጊውን ካፒታል ለማሰባሰብ /ለማሳደግ/ እና የኢንቨስተሮችን ፍላጎት ለመሳብ/ለመያዝ/ ውጤታማ መሳሪያ ነው፡፡ የንግድ ሥራ እቅድ የንግዱን ግባችና ዓላማዎች በግልፅና በተጨመቀ መልኩ የሚገልፅና ለእሱም ስኬት የአሰራር ስልቱን የሚያመለክት መሣሪያ ነው፡፡ እንዲሁም የንግድ ሥራ እቅድ ለአምራቾች/አገልግሎት ሰጭዎች ፍላጎት ላላቸው ኢንቨስተሮችና አቅራቢዎች ለንግዱ ግቦች የላቀ የመገናኛ መሣሪያ ነው፡፡
በርካታ የንግድ ሥራዎች በእቅድና በዝግጅት እጥረት ምክንያት ይወድቃሉ፡፡ ስኬታማ ለሆነ ንግድ ሥራ ከዚህ በታች የተዘጋጀው መመሪያ ለአምራቹ/ለአገልግሎት ሰጪው የንግድ እቅድ መረጃ ምን ያህል እንደሚያስፈልግ በበለጠ ለመረዳት ይረዳል፡፡ የመረጃው በዝርዝር መምሪያ ትክክለኛ መሆን፣ ተቋማት፣ ባንኮች፣ ኢንቨስተሮችና አቅራቢዎች ድጋፍ ሲጠይቅ ፈጥኖ ምላሽ ለመስጠት ያመቻል፡፡ በአጠቃላይ አምራቹ/አገልግሎት ሰጭው ራሱ የንግድ እቅድ ለማዘጋጀት ኃላፊነት አለበት፡፡
የንግድ እቅድ ንግዱ ምን እንደሚሰራ፣ እንዴትና የት እንደሚሰራ አና የንግዱ ካፒታል እንዴት እንደሚገነባና እንዴት እንደሚመራ የሚከተሉትን ምዕራፎች ጨምሮ መሰረታዊ ክፍሎቹን ያብራራል፡፡
• ግላዊ መረጃዎች
• ያሉና የሚገዙ የመሥሪያ መሣሪያዎች
• ስራው የሚካሄድበት ህንፃና መሬት
• የዓመታዊ ምርቱ/አገልግሎት እቅድ
• ለዓመት የሚያስፈልጉ ጥሬ እቃዎች
• ዓመታዊ የሽያጭ እቅድ
• ሌሎች ዓመታዊ የስራ ማስኬጃ ወጭዎች
• የዓመታዊ ትርፈና ኪሳራ መግለጫ
የራሳችሁን የንግድ እቅድ ለመስራት የሚጠቅማቹ የንግድ እቅድ መስሪያ የሚሆን ፎርም ነፃ ጠቃሚ ሰነዶች የሚለው ክፍል ውስጥ ስላለ ዳውሎድ አድርጋቹ መጠቀም ትችላላቹ ፡፡