የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

የቢዝነስ ማማከር

አዲስ ቢዝነስ የመጀመር ፍላጎት ካለዎት ሃሳብ አይግባዎት አጅግ ብዙ ቁጥር ያላቸውና በሳይንሳዊ ጥናት የተደገፉ የቢዝነስ ዕቅዶችና ፕሮጀክቶችን በሚገባ አዘጋጅተን እንጠብቅዎታለን፡፡ ወይም ደግሞ ፍላጎትዎ ነባር ቢዝነስዎን ማስፋፋትና ማሻሻል ከሆነም ለዚህም መፍትሄች አሉን፡፡

የፕሮጀክትና የአዋጪነት ጥናቶች

እንደ ወተትና ስጋ ልማት፣ የዶሮ እርባታ፣ የእርሻ ልማት፣ ሆቴል፣ ሎጅ፣ የድግስ ዝግጅት፣ የቀንድ ከብት ማደለብ፣ የጂፕሰም ምርት፣ የሸክላ ንጣፍ እና የወረቀት ምርት ያሉ የቢዝነስ ዘርፎች አዳዲስና የማስፋፊያ ፕሮጀክቶች እና የአዋጪነት ጥናቶችን እናዘገጃለን፡፡ የፕሮጀከት እና የኣዋጭነት ጥናታችን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ የሚዘጋጅና የደንበኞቻችንን እርካታ ያማከለ እነዲሆን በጥናቱ ላይ የሚሳተፈው ቡድን በዘርፋቸው ከፍተኛ እውቀትና የካበት ልምድ ባለቸው ባለሙያች የተዋቀረ ነው፡፡ በመሆኑም የጥናት ዝግጅታችን ጥራት እንዲኖረውና ውጤታማ ይሆን ዘንድ የእነዚህ ትጉ ባለሙያዎች ቁጥጥርና ክትትል አይለየውም፡፡

የቢዝነስ ስልጠና

የቢዝነስ ልማት፣ የፋይናንስ አጠቃቀም እና ወደአዲስ ቢዝነስ ለመግባት የሚረዱ የቢዝነስ እቅዶች በሳይንሳዊ መንገድ እንዴት ይዘጋጃሉ እንዲሁም ነባር ቢዝነስን እንዴት ወደመካከለኛ እና ትልቅ ቢዝነስ ማሳደግ ይቻላል በሚሉ የቢዝነስ ጉዳዮች ላይም ስልጠና እንሰጣለን። በተጨማሪም የጊዜ አጠቃቀም፣ የአመራር ክህሎት፣ የቢዝነስ አዕምሯዊ ዝግጅት እና ሌሎች የቢዝነስ ዘርፎችም የሥልጠናዎቻችን አበይት ርዕሰ ጉዳዮች ናቸው። የስልጠናዎቻችን ተሳታፊ ይሁኑ ለብዝነስዎ ወሳኝ የሆኑ መሰረታዊ ነገሮችን መረዳት እንድትችሉ እናግዛችኋለን። ከዚህ ሁሉ በላይ ግን ለምንሰጣቸው ስልጠናዎች በቂ የስልጠና ዝግጅት አድርገን እንጠብቅዎታለን። ውጤታማ እና ዘላቂ ቢዝነስ መፍጠር የምትችሉበትን ወሳኝና መሰረታዊ ክህሎቶችንም መጨበጥ እንድትችሉ እንረዳችኋለን። ቢዝነስዎ ነባራዊ ሁኔታን ያገናዘበና ተጨባጭ ሊሆን ይገባል። የሙያ አገልግሎትን የመሸጥና አትራፊ ያላማድረግ ዋነኛው ችግር ባለሙያዎችን ነጋዴ/ሻጭ አድርጎ ያለማብቃትና ያለማልማት ችግር ነው። እናም እኛ በዚህ ላይ ስኬታማ እንዲሆኑ የቢዝነስ ልማት እና ደንበኛ ተኮር የሆነ ቢዝነስ ክህሎትን እናስጨብጥዎታለን። ከቢዝነስ እድገት ባለሙያ አንስቶ እስከደንበኛ ግንኙነት ባለሙያ ድረስ ሁሉም የቢዝነስዎ ባለድርሻ በቢዝነስ ልማት ላይ ተሳታፊ መሆን ይኖርበታል። በሁሉም የቢዝነስዎ መዋቅር ላይ የቢዝነስ ልማት ባህል እንዲያዳብሩ እናግዝዎታለን።

ከላይ ያሉትን አገልግሎቶችን ለማግኘት ከፈለጉ

በ ኢሜይል አድራሻችን ፦ info@yerasbusiness.com
በስልክ ቁጥራችን ፦ 0913014229/0911702657

ጤና ይስጥልኝ
አዳዲስ የቢዝነስ መረጃዎችና ዶክመንቶች ሲመጡ እንዲደርስዎ ይመዝገቡ
ጤና ይስጥልኝ
አዳዲስ የቢዝነስ መረጃዎችና ዶክመንቶች ሲመጡ እንዲደርስዎ ይመዝገቡ
select another Language »