አዋጭ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር

   አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር

አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር የሚሰጣቸው አገልግሎቶች

ቁጠባን ባህል አድርጎ ከሌላ ወገን በሚገኝ የገንዘብ ምንጭ ሳይሆን በተቆጠበ የራስ ገንዘብ ህይወትን መቀየር፣ ለውጥ ማምጣት ይቻላል ብሎ የሚያምነው አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/ኅ/ስራ ማህበር መደበኛና የፈቃድ ቁጠባ ለአባላቶቹ ያዘጋጀ ሲሆን አባላቶቹ ሼር በመግዛት አባል ከሆኑ በኃላ ቁጠባን ይጀምራሉ፡፡ ለስድስት ወር በተከታታይ በመቆጠብ የቁጠባ ባህላቸውን ካዳበሩ በኃላ ወደ ብድር እንዲሄዱ በማድረግ የራሳቸውን፣ የቤተሰባቸውን ብሎም የአገራቸውን እድገትና ለውጥ እንዲያፋጥኑ ድጋፍ ያደርጋል፡፡

•የኅብረት ሥራ ማህበሩ መነሻ ወይም ዝቅተኛ መደበኛ ቁጠባ መጠን ከ30 ቀናት (ከአንድ ወር) ገቢ ውስጥ 10 በመቶ ወይም ብር 350.00 (ሦስት መቶ ሃምሳ) ነው፤

• እያንዳንዱ አባል ከመነሻ የቁጠባ መጠን በተጨማሪ የፍላጎት ቁጠባ፣ የጊዜ ገደብ ተቀማጭ እና የተለያዩ ቁጠባዎችን መቆጠብ ይችላል፤

የፍላጎት ቁጠባ፡- መደበኛ መቆጠብ ካለበት 350 ብር ወይም ከገቢው 10 በመቶ በተጨማሪ የሚቆጠብ ቁጠባ ነው፡፡

የጊዜ ገደብ ቁጠባ፡-ኅብረት ስራ ማህበሩ እንደአስፈላጊነቱ ከአባላቱ ጋር በሚያደርገው ስምምነት  መሠረት ለተወሰነ ግዜ ለአስቀማጩ ተከፋይ የማይሆን የጊዜ ገደብ ቁጠባ ሊሰበስብ ይችላል

ተ.ቁ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ቁጠባ የሚቀመጥበት ግዜ የሚከፈል ወለድ መጠን በፐርሰንት
አስከ
1 50,000.00 500,000.00 6 ወር 8.5
2 50,000.00 500,000.00 12 ወር 9.0
3 500,000.00 በላይ 6 ወር 9
4 50,000.00 500,000.00 ከ 18 ወር አስከ 24 ወር 10
5 500,000.00 በላይ 12 ወር 10
6 50,000.00 500,000.00 ከ 30 ወር በላይ 11
7 50,000.00 በላይ ከ 24 ወር በላይ 11

• ማንኛውም አመልካች አባል እንዲሆን ከተፈቀደለት ዕለት ጀምሮ ያለማቋረጥ በተከታታይ በየወሩ መደበኛ ቁጠባ መቆጠብ ይኖርበታል፤

• የትኛውም ቁጠባ አባልነት በሚቋረጥበት ወቅት ተመላሽ ይሆናል፤

• አባሉ የፍላጎት ቁጠባ ማውጣት ከፈለገ በፅሁፍ ወይም ኅብረት ሥራ ማህበሩ ባዘጋጀው ፎርም በመጠየቅ ማውጣት ይችላል። ሆኖም ተበዳሪ ወይም ዋስ ከሆነ ብድሩ ተከፍሎ ካላለቀ ወይም ዋስትናው ካልተነሳ ማውጣት አይቻልም፤

• አባሉ በፍላጎት ያስቀመጠውን የፍላጎት ቁጠባ፤ የተበደረው ብድር ቀሪ ዕዳው የፍላጎት ቁጠባውን ያህል ከሆነና ቁጠባው ለሌላ ተበዳሪ በዋስትና ካልተያዘ የፍላጎት ቁጠባውን ማጣጣት ይችላል፤ • አባሉ ያለውን መደበኛ ቁጠባ ማውጣት የሚችለው ከአባልነት ሲለቅ ብቻ ነው።

2,ብድር

የአባላት የብድር ዓይነትና መጠን የሚሰጠው የብድር ዓይነት፣ መጠንና የቆይታ ጊዜ ዝርዝር፡

አዋጭ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሰረታዊ የኅብረት ሥራ ማህበር ከአባላት መደበኛ እና የፍላጎት ቁጠባ ከአባላት ያሰባሰበውን ገንዘብ በኅብረት ሥራ ማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ/በተወካይ አባላት በየጊዜው በሚሰጥ ውሳኔና በመተዳደርያ ደንብና በብድር መመሪያው በተቀመጠው መሠረት ለአባላት ብድር በመስጠት አባላት በፍላጎታቸው በሚመርጡዋቸው የተለያየ የሥራ መስክ በመሰማራት የገቢ ምንጫቸውን እንዲያሰፉና ኑሮአቸው እንዲሻሻል በማድረግ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል:: በመሆኑም ለአባላቱ የመደበኛ ብድር፣ የቤት (ግዥ፣ እድሳትና ግንባታ) ብድር፣ ለቤት መኪና ግዢ ብድር እና ለንግድ መኪና ግዢ ብድር ይሰጣል።  በችሎታው ለኅብረት ሥራ ማህበሩ አስተዋጽኦ ማድረግ፤

 

ተ.ቁ የብድር አይነት የብድር መጠን በብር እስከ ቅድመ ብድር የቁጠባ መጠንና ጊዜ የብድር ወለድ መጠን የብድር ውል ጣራ
በመቶኛ በብር አስከ ጊዜ
1 መደበኛ ብድር
ለማህበራዊ ግልጋሎት 100 ሺ 25 25,000.00 6 ወርና ከዚያ በላይ 13.5 3 ዓመት
ለትምህርትና ለጤና 100 ሺ 25 25,000.00 6 ወርና ከዚያ በላይ 13.5 3 ዓመት
ለንግድ 300 ሺ 25 75,000.00 6 ወርና ከዚያ በላይ 13.5 3 ዓመት
2 ለቤት መኪና ብደር 600 ሺ 40 240,000.00 1 ዓመትና ከዚያ በላይ 14.5 5 ዓመት
3 ለንግድ መኪና ብድር 800 ሺ 40 320,000.00 1 ዓመትና ከዚያ በላይ 14.5 5 ዓመት
4 የቤት ብድር
ለቤት ግዢ 1 ሚሊዮን 30 300,000.00 1 ዓመትና ከዚያ በላይ 15.5 10 ዓመት
ለቤት ማደሻ
ለቤት ግንባታ

3, የልጆች ቁጠባ

አመለካከትን መቀየር ነገን መቀየር ነው!!!

አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የህብረት ስራ ማህበር የተመሰረተው አባላት ካላቸው ገንዘብ ላይ በመቆጠብ እና ብድር በመውሰድ ህልማቸውን እንዲያሳኩና የገንዘብ ችግሮቻቸውን እንዲፈቱ ለማስቻል ነው፡፡ ለዚህም አዋጭ በ33 ሴቶችና በ8 ወንዶች በመመስረተ ለአባላቶቹ የቁጠባና የብድር አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ የህብረት ስራ ማህበር ነው፡፡ ከ2007ዓ.ም. ጀምሮ ደግሞ አገልግሎቱን በማስፋት የልጆች ቁጠባን የጀመረ ሲሆን ልጆች በለጋ ዕድሜያቸው የቁጠባ ባዕልን እንዲያዳብሩ ለማበረታታት ታስቦ ነው፡፡ ልጆች የሚያገኙትን የኪስ ገንዘብ፣ ወላጆች/አሳዳጊዎች ለልጆቻቸው ለተለያዩ ወጪዎች  የያዙትን በጀት ቁጠባን ከግንዛቤ ውስጥ ያስገባ እንዲሆንም አዋጭ የተለያዩ እገዛዎችንና ስልጠናዎችን ይሰጣል፡፡ ከቁጠባ በተጨማሪ ልጆች ገንዘብን/ሀብትን በአግባቡ መጠቀምንና ማካፈልን ወይም መርዳትን እያውቁ እንዲያድጉ ሶስት የገንዘብ ማጠራቀሚያዎችን በመስጠት  ቁጠባን፣ በአግባቡ ገንዘብን/ሀብትን መጠቀምን እና ማካፈልን ለወላጆች/አሳዳጊዎች ግንዛቤውን በማስጨበጥ ላይ ይገኛል፡፡

የልጆች ቁጠባ ደብተርን ለመክፈት ወላጅ/አሳዳጊ የራሱንና ልጁን ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ በመያዝ ወደ አዋጭ ቢሮዎች በመምጣት መመዝገብ የሚቻል ሲሆን መቆጠብ የሚፈልጉትን የገንዘብ መጠን መቆጠብ ይችላሉ፡፡ ይህም ልጆችን ከማበረታታቱም በተጨማሪ ለወጣትነት ዕድሜያቸው የዩኒቨርሲቲ ወጪቸውን መሸፈኛ ወይም ጥሩ የስራ መነሻ ሊሆናቸው ይችላል፡፡ በተጨማሪም ከህብረት ስራ ማህበሩ 10% የተቀማጭ ገንዘብ ወለድ ያገኛሉ፡፡

የብድር መስፈርቶች

 • ተቀጣሪ ሠራተኛ ከሆነ ገቢውን የሚገልጽ ከሚሰራበት መስሪያ ቤት ወይም ድርጅት ደብዳቤ ማቅረብ
 • ነጋዴ ከሆኑ የንግድ ፈቃድና ግብር ከፋይ የሆኑና የገቢና ወጪ መግለጫ ማቅረብ
 • ለብድሩ ተመጣጣኝ የሆነ ዋስትና ማቅረብ
 • 1% የህይወት መድን ዋስትና የሚከፍል
 • 1% የአገልግሎት የሚከፍል
 • ያገባ ወይም ያላገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ፤ ባለትዳር ከሆኑ ሁለቱም በአካል የሚገኙ
 • የብድር ማመልከቻ በአካል ተገኝቶ በተዘጋጀው የማህበሩ ብድር ማመልከቻ መሙላት

የብድር ዋስትና አይነቶች

 • በቁጠባ ዋስትና የሚሰጥ ብድር የአባሉ ቁጠባና የዋሱ ቁጠባ ተደምሮ ያለውን ቁጠባ ያህል ያለ ተጨማሪ ዋስ የሚሰጥ ብድር ነው
 • በደብዳቤ ዋስትናና ከአባል አንድ ሰው ቁጠባ ያለው በማቅረብ የሚሰጥ ብድር
 • በንብረት ዋስትና የሚሰጥ ብድር
 • የቤት ካርታ እና የሚኪና ሊብሬ የተገዛ ወይም የሚገዛ፣ ሊብሬ ከሆነ መኪናው ከተመረተ 15 ዓመት ያልሆነው መሆን አለበት
 • ማንኛውም ብድር የሚሰጠው የተበዳሪውን የመክፈል አቅም ያገናዘበና ባቀረበው ዋስትና መጠን ብቻ ነው

የብድር ጣሪያ

 • የብድር ጣሪያው አስከ 1000000.00/ አንድ ሚሊየን ብር ድረስ ወለድ
 • ለመደበኛ ብድር ለወንድ 13.5 እንዲሁም ለሴት 13.0
 • ለመኪና 14.5
 • ለቤት 15.5

የብድር ጊዜ

 • ለመደበኛ – 3 ዓመት
 • ለመኪና – 5 ዓመት
 • ለቤት- 10 ዓመት

  አባልነት

  የኅብረት ስራ ማኅበራችን አባል ለመሆን የሚያበቁ መስፈርቶች

  • በሕግ መብቱ ያልተገፈፈ
  • ዕድሜው 18 ዓመት የሞላው እና ከዚያ በላይ የሆነ ዕድሜው ከ18 ዓመት በታች ከሆነ በህፃናት ቁጠባ
  • የመመዝገቢያ ክፍያ ብር 1000፣ የዕጣ (ሼር) ሁለት እጣ ብር 2000 እና መደበኛ ቁጠባውን ብር 300 ወይም የደሞዙን 10% መቆጠብ የሚችል
   በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የአራጣ አበዳሪ ያልሆነ
  • የማኅበሩን አላማና ደንብ የተቀበለና ግዴታውን ለመፈጸም ፈቃደኛ የሆነ
  • በማህበሩ የሥራ ክልል ውስጥ የሚኖርና ገቢ ያለው
  • የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ፎቶ ኮፒ
  • ሁለት ጉርድ ፎቶ ግራፍ

  አባል ለመሆን መሟላት የሚገባቸው፣

   1. የአባልነት መመዝገቢያ ክፍያ

  የመመዝገቢያ ክፍያ በአንድ ጊዜ የሚከፈል 1000 ብር ነው

   1. ዕጣ (ሼር)

  የአንድ ዕጣ (ሼር) መጠን ብር አንድ ሺ ሲሆን አንድ አባል ቢያንስ ሁለት እጣ ሁለት ሺህ ብር መግዛት አለበት

   1. መደበኛ ቁጠባ

  ማንኛውም አባል በወር ቢያንስ ሶስት መቶ አምሳ ብር መቆጠብ አለበት

   1. የፍላጎት ቁጠባ

  አንድ አባል ከመደበኛ ቁጠባ በተጨማሪ የፈለገውን/ችውን የገንዘብ መጠን በፍላጎት መቆጠብ ይችላል፡፡ የፍላጎት ቁጠባው አባሉ በፈለገው ጊዜ ወጪ ሊደርገው ይችላል፡፡

  አድራሻ

  ዋና መስሪያ ቤት – አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 7
  ቤልኤር አካባቢ ከግሪን ቫሊ ሆቴል አጠገብ
  ስልክ: +251-118-12-44-44
  ኢሜይል: generalmanager@awachsacc.com
  ዌብሳይት: www.awachsacc.com
  አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

ጤና ይስጥልኝ
አዳዲስ የቢዝነስ መረጃዎችና ዶክመንቶች ሲመጡ እንዲደርስዎ ይመዝገቡ
ጤና ይስጥልኝ
አዳዲስ የቢዝነስ መረጃዎችና ዶክመንቶች ሲመጡ እንዲደርስዎ ይመዝገቡ
select another Language »